የቻድ ወታደራዊ መንግስት እና ተቃዋሚ ቡድኖች የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ቢያንስ 40 የሚሆኑ ቡድኖች ከመንግስት ጋር ለሀገራዊ ምክክር ስምምነት የፈረሙ ሲሆን ፣ዋነኛዉ የሽብር ቡድን ግን ስምምነቱ ላይ እንደማይሳተፍ ገልጿል፡፡

በኳታር ዶሃ የተፈረመዉ ይህ ስምምነት በነሀሴ 20 ለሚካሄደዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መንገድ የሚከፍት ነዉ ተብሎለታል፡፡

ከጥር ጀምሮ ኳታር በማሀማት ኢድሪስ ዴቢ በሚመራዉ ወታደራዊዉ መንግስት እና በተቃዋሚ ሀይሎች መካከል ጣልቃ በመግባት ስታደራድር ቆይታለች፡፡

ይሁን እንጂ የቻድ መንግስት ከፍተኛ ተቃዋሚ የሆነዉ የሽብር ቡድን፣ ከዚህ ሁሉ ልፋት በኋላም የሰላም ስምምነቱን እንደማይቀበል አስታዉቋል፡፡

ከ1ሺህ 500 እስከ 2 ሺህ ተዋጊዎች ያሉት ቡድኑ፣ ለ30 ዓመታት ቻድን የመሩት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ግድያን መምራቱንም የአልጀዚራ ያመለክታል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ነሃሴ 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.