ኬንያውያን ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቷን የሚመራውን ፕሬዚዳንታቸውን ዛሬ መምረጥ ጀምረዋል፡፡

በመላው አገሪቱ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የምርጫ ጣቢያዎች የተከፈቱ ሲሆን ድምጽ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ለፕሬዚዳንትነት እየተወዳደሩ ያሉት የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን፣በኬንያ ሪፍት ቫሊ ክልል በሚገኘው ኮሳሼይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡

የፕሬዚዳንት ዕጩ ራይላ ኦዲንጋ ጋር አብረው እየተወዳደሩ ያሉት ማርታ ካሩዋ በኬንያ ማዕከላዊ ግዛት ኪሪያኒጋ ግዛት ውስጥ መስጠታቸዉም ተነግሯል፡፡

እስካሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች እስከ አመሻሹ 11 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆነዉ ይቆያሉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.