የተባበሩት መንግስታት የጸጥታዉ ምክር ቤት በጋዛ ጦርነት ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል፡፡

ስብሰባዉ በርካታ አባላት በእስራኤልና በፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ከደረሱበት የተኩስ አቁም ስምምነት በኃላ እስራኤል ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ በአካባቢው ላይ ስጋት መፍጠሩን ተከትሎ ነዉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የመካለኛዉ ምስራቅ ተወካይ ቶር ዌስላንድ የትኛዉም የእርስ በርስ ጦርነት ለእስራኤልም ሆነ ለፍልስጤም ከባድ መዘዝን እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱም ደካማ ነዉ ሲሉ ተችተዋል፡፡
የሩሲያ አማባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዚያ ምክር ቤቱ ይህ ሁኔታ በጥልቅ ያሳሰበዉ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ተጀምሮ የነበረዉ ወታድራዊ ግጭት እንዲቀጥልና ቀደም ሲል በጋዛ የነበረዉ አስከፊ የሰብአዊ ሁኔታ እንዲባባስ ሊያደርግ እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

እስራኤል ባሳለፍነዉ አርብ በጋዛ ሰርጥ ላይ ባደረገችዉ ተከታታይ የቦምብ ድብደባ ቢያንስ 44 ፍልስጤማዉያን ንጹሀን ዜጎች መገደላቸዉንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸዉን የፍልስጤም ጤና ሚንስተር ገልጸዋል፡፡

የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን በምላሹ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ቢተኩስም አብዛሃኛዎቹ ኢላማቸውን ሳቱ ናቸው ተብሏል፡፡

በቤዛዊት አራጌ

ሐምሌ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *