የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው::

ከጳጉሜ 2 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ይቆያል የተባለው አለም አቀፍ ኤክስፖው፣ ዘመኑ የደረሰባቸውን ቴክኖሎጂዎች ለማስተዋወቅ የታቀደበት መሆኑን አዘጋጆቹ አስታዉቀዋል፡፡

በሮቦቲክስ፣ ኤሌክትሮኒክስ ክፍያዎች እና ቴክኖሎጂ ላይ የተሰማሩ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ድርጅቶችም እንደሚሳተፉበት ተጠቁሟል፡፡

በሶላር፣ ሳይበር ደህንነት፣ በግብርና እንዲሁም የቴሌኮም ዘርፉን ጨምሮ በ14 አይነት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል፡፡

ከአፍሪካ፣ አዉሮጳ፣ እስያ እና የሰሜን አሜሪካ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ይሳተፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ኤክስፖ፣ ከ500 በላይ ድርጅቶች እንደሚመዘገቡ እና ከ45 ሺህ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅም ሰምተናል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ እንደዚህ ያሉ አለም አቀፍ መድረኮች ለሃገር መልካም ገፅታ ግንባታ ከሚኖራቸው ሚና ባሻገር የአፍሪካዊያንን ትብብር እና ትስስር እንደሚያጠናክር ተጠቁሟል፡፡

የቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግር ከዘርፉ ጋር ያለንን ግንኙነት ማሻሻል ይገባናል ያሉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ተቋማትም ለእንግዶች የተሻለ አገልግሎት እንዲያቀርቡ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

ከኤክስፖው በተጓዳኝ በተጋባዥ እንግዶች የሚቀርብ ሲምፖዚያም ማዘጋጀቱም ተነግሯል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ሐምሌ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.