እስራኤል ጦር በናባል ወረራ የአል አቅሳ ብርጌድ አዛዥን መግደሉ ተሰምቷል፡፡
የፍልስጤም ጤና ጠበቃ ሚንስተር አንድ የታጠቁ ከፍተኛ አዛዥን ጨምሮ ሶስት ፍልስጤማዉያን በናባል ከተማ በእስራኤል ወታደሮች መገደላቸዉን ተናግረዋል፡፡
የእስራኤል ጦር በጥንታዊቷ ከተማ የሚገኘዉን ህንጻ ከቦ ለረጅም ሰአት የቆየ የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉን ተከትሎ ነዉ የአል አቅሳዉ ብርጌድ አዛዥ ኢብራሂም አል ናቡሲ ጦርነቱን የተቀላቀሉት ተብሏል፡፡

የ30 አመቱ አል- ናቡሲ ከ32 አመቱ እስላም ሳቡሀ እና ሁሴን ጋር መገደሉን ብሎም ከ 60 የሚበልጡ ሰዎች መቁሰላቸዉን የፍልስጤም ጤና ጥበቃ ሚንስተር አስታዉቋል፡፡
የናባል አምበሳ በመባል የሚታወቀዉ አል- ናቡሲ ከብዙ የግድያ ሙከራዎች መትረፉን አንስተዉ እስራኤል አል ናቡሲ ላይ የግድያ ሙከራ ስታደርግ ይህ የመጀመሪያዋ እንዳልነበር የአልጀዚራዉ ጆን ሆልማን ተናግሯል፡፡
የእስራኤል ወታደሮችም አሸባሪዉ ኢብራሂም አል-ናቡሲ በናል መገደሉን አረጋግጠዋል፡፡
በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 03 ቀን 2014 ዓ.ም











