ኢትዮጵያ በክብር እንግድነት የተጋበዘችበት የንግድ ፎረም በቱርክ ሊካሄድ ነው፡፡
ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው የቱርክ አፍሪካ ንግድ ፎረም ኢትዮጵያ በልዩ የክብር እንግድነት ትሳተፋለች ተብሏል፡፡
የቱርክ አፍሪካ ንግድ ፎረም በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ በመጪው መስከረም 14 እና 15 ቀን 2022 እንደሚካሄድ የቱርክ ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ትብብር ፎረም ፕሬዝዳንት ኡታኩ ብኒጊሱ ተናግረዋል።
በፎረሙ ከ1 ሺህ 250 በላይ በንግድ እና ቢዝነስ የተሰማሩ አፍሪካዊያን እንደሚሳተፉ ገልፀው፤ ኢትዮጵያም በዘንድሮው ዓመት በሚካሄደው ፎረም በእንግድነት እንደምትሳተፍ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም በፎረሙ ለሚሳተፉ አንድ መቶ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የንግድና ቢዝነስ ሰዎች ልዩ የአገልግሎት ቅናሽ ይደረግላቸዋል ነው ያሉት፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቱርክና አፍሪካ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱ ይታወቃል ባሁኑ ሰአት እንኳን ቱርክ በ43 የአፍሪካ ሀገራት ኤምባሲዋን ከፍታ እየሰራች ትገኛለች፡፡
ከአለም ሀገራት 19ኛ የኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ቱርክ ወደ 4ሚሊዮን የሚጠጉ የንግድ ካምፓኒዎች እንዳሏት ነው የሚነገረው፡፡
እንደዚሁም ወደ 350 የሚጠጉ የአንዱትሪ ፓርኮች በሀገሪቷ እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም











