የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የተላለፉ መልዕክቶች፡-

ዛሬ የሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጫ ማብሰሪያ ስነስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተናገሩት፡-

• ሀገርን በፀና መሰረት ላይ ማቆም የዚህ ትውልድ ሃላፊነት ነው
• ይህ ትውልድ አባቶቻችን ያሰቡትን ህልም እና ፍላጎት እውን በማድረግ ሀገርን በፀና መሰረት ላይ የማቆም ሃላፊነት እንዳለበት ሊገነዘብ ይገባል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

• በታሪክ ውስጥ ማለፍ እና ታሪክ መስራት ይለያያል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ “በታሪክ ውስጥ ማለፍ እድል፤ ታሪክ መስራት ደግሞ ድል ነው” ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሀሮ ከተናገሩት ፦

• ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዚህ በያዝነው ዓመት በ2014 ለማከናወን ከተያዙ አብይ እቅዶች መካከል በሁለት ዩኒት ማለትም በሁለት ታርባይንና ጀነሬተሮች ኃይል ማመንጨት አንዱ ሲሆን ይህ እቅድ ተሳክቶ በ2ቱም ዩኒቶች ኃይል ማመንጨት ተችሏል።

• ከለውጡ በኃላ በፕሮጀክቱ ላይ የማስተካከያ እርምጃ ከተወሰደ በሶስት ዓመታት ውስጥ በግድቡ ውስጥ መተከል የነበረባቸው የውሃ ማስተላለፊያ የብረታብረት ስራዎችን በማጠናቀቅ የመካከለኛውን የግድብ ከፍታ ከሃያ አምስት ሜትር ወደ መቶ ሜትር ማድረስ ተችሏል።

• እንደዚሁም የግድቡን ግራና ቀኝ በትንሹ እስከ ስድስት አርባ አምስት የደረሰም አለ ወይም ከባህር ጠለል በላይ እስከ ስድስት አርባ አምስት ወይም መቶ አርባ አምስት ሜትር ከመሰረት ከፍ ያለ በተጨማሪ በትንሹ እስከ መቶ አስራ አንድ ሜትር ከፍ በማድረግ ሁለት ሙሊቶችን ማከናወን የተቻለ ሲሆን ሶስተኛውሙሊትበሂደት ላይ ይገኛል ።

• ከምንም ደረጃ ተነስቶ ሁለት ተርባይኖች እና ጄነሬተሮች በመትከል ኃይል ማመንጨት ተችሏል።

በአባቱ መረቀ
ነሃሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.