የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት ለምን ተቋረጠ?

ከሰአታት በፊት የቴሌቪዥን ጣበያዎች ሙሉ ስርጭት ተቋርጦ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ ስርጭት የሚሰጡ የቴሌቪዥን ጣበያዎች ለተወሰነ ሰአት ስርጭታቸው ተቋርጦ ነበር፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን ጠይቋል፡፡
የባለስልጣኑ የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ደሴ ከፈለ ለጣበያችን እንደተናገሩት በቴሌቪዥን ጣበያዎች ላይ የቴክኒክ ብልሽት አጋጥሞ ነበር ብለዋል፡፡
አሁን ላይ ግን የተከሰተውን የቴክኒክ ብልሽት ተስተካክሎ ስርጭት ጀምረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.