የዉጭ አገር ዜጎች ምዝገባ፡-

የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ የሚገኙ የዉጭ አገር ዜጎች በቀጣዮቹ ስምንት ቀናት ዉስጥ እንዲመዘገቡ አሳሰበ፡፡

የውጭ ሀገራት ዜጎችን ህጋዊ የማድረግ ምዘገባው እስከ ነሐሴ 13 ቀን መራዘሙን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡
በአገሪቱ የሚገኙ የዉጭ አገር ዜጎች በቀጣዮቹ ስምንት ቀናት ዉስጥ እንዲመዘገቡ እድል መሰጠቱን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ተናግረዋል፡፡

እስካሁን በተካሄደ ምዝገባ በኢትዮጲያ የሚኖሩ 70 ሺህ የውጭ አገራት ዜጎች መመዝገባቸዉን ቃል አቀባዩ አስታዉቀዋል፡፡
ምዝገባው የተራዘመበት ምክንያት በቀነ ገደቡ በተለያዩ ምክንያቶች ያልተመዘገቡ የዉጭ ሀገራት ዜገች ዕድሉን ለመስጠት እንደሆነ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

መንግስት የሰጠዉ ዕድል ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠ እንደሆነም ነዉ አምባሳደር መለስ የተናገሩት፡፡

እስካሁን ድረስ በተደረገው ምዝገባ ከ 36 ሀገራት የመጡ ከ70 ሺህ በላይ የውጭ ሀገራት ዜጎች መመዝገባቸዉም ታዉቋል።

በአባቱ መረቀ
ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.