ሞስኮ በኢራን የኒዉክሌር ስምምነት ላይ ያላት ሁለተኛ እቅድ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለዉ አስታወቀች::

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተባበሩት መንግስታት የጸጥታዉ ምክር ቤት የሰጠዉን የመግባባት ዉሳኔ የሚጥስ እና ለመላዉ መካከለኛዉ ምስራቅ የማይቀር አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረዉ አስታዉቀዋል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኢቫን ኔቻየቭ 2015ቱን ስምምነት በማንሳት፣ ማንኛዉም አይነት ሁለተኛ እቅድ የጸጥታዉ ምክር ቤት የጋራ የስምምነት ዉጤቶች እንደሚቃረን አንስተዉ፣ የኢራን የኒዉክሌር መርሃ-ግብር የዚያን አመት ስምምነት ይደግፋልም ብለዋል፡፡
ኔቻየቭ በቪየና በመካሄድ ላይ ባለዉ ምክክር የ2015ቱ ስምምነት ብቸኛዉ ዉጤታማ እና ምክንያታዊ አማራጭ እንደሆነ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

በቪየና በአሜሪካ እና በኢራን ልኡካን መካከል የተደረገዉ ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት ቀደም ሲል በድርድሩ ላይ የነበሩ መሰናክሎች ላይ የተወሰነ እድገት ያሳያል ብለዋል፡፡

ኔቻየቭ የዉይይቱ አዎንታዊ ዉጤት ሊደረስበት የሚችል መሆኑን በሚወያዩት ፓርቲዎች መካከል ያን ያህል የሃሳብ ልዩነት እንደሌለ አንስተዋል፡፡
ከዚህ በኋላ የሚመጣዉ እድገት በእያንዳንዱ ወገን ፖለቲካዊ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሞስኮ የአዉሮፓ ህብረትን የጉልበተኞች ስብስብ ነዉ፤ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሚባል ማሳሰቢያ በዚህ ሃሳብ ላይ ተቀባይነት አይኖረዉም በማለት ቃል አቀባዩ ፒተር ስታኖን፤ ቦሬልን ተችተዋል፡፡

ስታኖ በአዉሮፓ ህብረት ሸምጋይነት ከተጠናቀቀዉ ከቴህራንና በዋሽንተን መካከል የተደረገዉ የቅርብ ጊዜ ምክክር ከተጠናከረ በኋላ የመደራደሪያ ሃሳቦቹ በስምምነቱ ወስጥ ተካቷል በማለት ሰነዱ የመጨረሻ መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
የሩሲያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስታኖ በምክክሩ ዉስጥ የተሳተፉትን ሁሉንም ወክለዉ እንደዚህ አይነት መግለጫ መስጠት እንደማይችል አንስተዉ፣ የኢራን ዉል በመባል የሚታወቀዉ ሚዛናዊ እንጅ በጭካኔ የተሞላ አይደለም ማለታቸዉን የዘገበዉ አርቲ ኒውስ ነው፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ነሐሴ 06 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *