አፍሪካ የአየር ንብረት ለዉጥን ለመቋቋም ከሚያስፈልጋት ገንዘብ መጠን ላይ 12 በመቶዉን ብቻ እያገኘች እንደሆነ ተገለጸ፡፡

አፍሪካ የዓየር ንብረት ለዉጥን ለመቋቋም ከሚያስፈልጋት የገንዘብ ድጋፍ ዉስጥ እያገኘች ያለቸዉ 12 በመቶዉን ብቻ መሆኑን ትናንት የወጣ አንድ ጥናት አመላክቷል፡፡

ይህም ሀብታም ሀገራት በህዳር ወር በሚያደርጉት የዓየር ንብረት ለዉጥ ስብሰባ ላይ በደንብ እንዲያስቡበት የሚያደርግ ነዉ ተብሏል፡፡

አፍሪካ የዓየር ንብረት ለዉጥን ለመቋቋም በዓመት 250ቢሊዮን ዶላር የሚያስፈልጋት ሲሆን እንደ ሪፓርቱ ከሆነ ግን በ2020 በዓመት 29.5 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነዉ እርዳታ ያገኘችዉ፡፡

ሀብታም ሀገራት በ2009 በግብጽ የተወያዩበትን ለደሀ ሀገራት በየዓመቱ 100 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ እና ጉዳዩንም የዉይይት ማዕከል ለማድረግ የገቡትን ቃል መጠበቅ አልቻሉም በሚል ትችት እና ወቀሳ እየቀረበባቸዉ ይገኛል፡፡

በአፍሪካ በተለያዩ ክልሎች ላለዉ የዓየር ንብረት ለዉጥ ጉዳት ከፍ እና ዝቅ ማለት የመሰረተ ልማት፣ የገንዘብ ድጋፍ እና የመልካም አስተዳደር ዕጦት መኖሩ እንደምክንያት የሚነሳ ጉዳይ ነዉ፡፡

የጉዳት መጠኑ በይበልጥ በመካከለኛዉ አፍሪካ ከፍ ያለ እንደሆነ ያነሳዉ ሪፖርቱ ለዚህም የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣በስፋት የብድር አቅርቦት አለመኖር እንዲሁም በፖለቲካ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ መረጋጋት አለመኖሩ እንደምክንያት የሚነሳ ነዉ ፡፡

እንደ ዓለምዓቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ ከሆነ አፍሪካ የዓለምን አንድ አምስተኛዉን የህዝብ ቁጥር የያዘች ቢሆንም ግን ወደ ዓየር የምትለቀዉ የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን ግን ከ3 በመቶ በታች መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ነሐሴ 06 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *