የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሶስተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቀቀ::

የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሶስተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቆ ውሃ በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል፡፡

በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ከባህር ጠለል በላይ 6 መቶ ሜትር ከፍታ አልፎ የግድቡ ውሃ ወደታችኛው ተፋሰስ አገራት መሄዱን ቀጥሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የግድቡን ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ለማብሰር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገኝተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታትም የግድቡ ሙሌት በስኬት መከናወኑም የሚታወስ ነው፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ፣እንኳን ደስ አለን፡፡

ነሐሴ 06 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.