ሩስያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉ ፑቲን ተናገሩ፡፡

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቨላድሚር ፑቲን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያ የመገናኛ አውታሮች ባወጡት መረጃ መሰረት ፔዮንግያንግ እና ሞስኮ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት መንግድ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
የሩስያው ፕሬዝዳንት ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ሰሜን ኮሪያ ከጃፓን ነጻ የወጣችበትን 77ኛ የነጻነት ቀንን በማስመልከት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት መላካቸውን ተነግሯል፡፡

ፑቲን በመልዕክታቸው ሰሜን ኮሪያ በሩቅ ምስራቅ ያላትን ቀጠናዊ ተሰሚነት እና የበላይነት አጠናክራ ትቀጥላለች ያሉ ሲሆን፣ ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከር የቀጠናው ጸጥታ ማስጠበቅ እና በኢኮኖሚው ረገድ ተደጋግፎ መስራት ሁለቱ ሀገራት ትኩረት የሚያደርጉባቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል፡፡

የሰሜን ኮሪያ እና የሩስያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ እንደጀመረ ይነገራል፡፡
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሩስያ የአለምን ሰላም ከመጠበቅ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያረገች የምትገኝ ሀገር መሆኗን ገልጸዉ፣ ከሩስያ ጋር አብሮ መስራት እድለኝነት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ ዘርፎች ላይ በጋራ የሚሰሩ ሀገራት ሲሆኑ በተለያዩ ጊዜያትም ወታደራዊ ለምምዶች ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበዉ፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሐሴ 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *