ዊሊያም ሩቶ የኬንያ ፕሬዝዳንት ሆነዉ ተመረጡ፡፡

ከፍተኛ ትንቅንቅ በተስተዋለበት የኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ዊልያም ሩቶ አሸናፊ መሆናቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ሩቶ ያሸነፉት ከተሰጠው ጠቅላላ ድምፅ 50.49% በማግኘት ሲሆን ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ራይላ ኦዲንጋ 48.8% ድምፅ ማግኘታቸውን ኮሚሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡

የ77 አመቱ ራይላ ኦዲንጋ ካለስኬት ለፕሬዝደንትነት ሲወዳደሩ ይህ ለአምስተኛ ግዜያቸው እንደሆነ የሚታወስ ሲሆን ይህ የመጨረሻቸው እንደሆነም ከዚህ ቀደም ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

ከፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ቅራኔ ውስጥ የሰነበቱት ምክትላቸው ዊልያም ሩቶ፣ በመጀመርያው የፕሬዝደንትነት የምርጫ ፉክክራቸው በከፍተኛ ትንቅንቅ አሸናፊ መሆናቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ነሐሴ 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *