ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፏል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ካላንደራቸው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ታሳቢ ያደረገ መሆን እንደሚገባው ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ ከመስከረም 28 – ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ እና ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እና የምግብ አቅርቦት ዝግጅት እንዲደረግም ትእዛዝ ተላልፏል።
ከፈተና ደህንነት እና አቅርቦት ጋር በተያያዘ የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት የሚመራ ዋና ግብረ ሃይል እንዲሁም በየካምፓሶቹ ካምፓስ ሃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ ሃይል እንዲደራጅ መመሪያ ተላልፏል፡፡
የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30,2015 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወሳል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም











