በቅርቡ በሩስያ ቁጥጥር ስር የሆነችዉ የዪክሬኗ ዶኔስክ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ጥብቅ ግንኙነት መፍጠር እፈልጋለዉ አለች::

በቅርቡ በሩሲያ ቁጥጥር ስር የገባችዉ የምስራቃዊ ዩክሬን ክፍል ዶኔስክ፣ ከሰሜን ኮሪያዉ ኪም ጆንግ ኡን ጋር አብሮ የመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች፡፡

ፒዮንግያንግ በሩሲያ የተያዙ ክልሎችን መልሶ ማቋቋም ስራዎችን ለመስራት እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች፡፡

የዶኔስክ ግዛት አስተዳዳሪ ዴኒስ ፑልሽን በጻፉት ደብዳቤ በሞስኮ በሚደገፈዉ ሪፐብሊክና ሰሜን ኮሪያ መካከል ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን እንፈልጋለን ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡

ዴኒስ ፑለሽን ደብዳቤያቸዉን ለኪም ጆንግ ኡን የላኩት በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ኮሪያ ከጃፓን ቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችበት ተሪካዊ ቀን ላይ ነዉ፡፡
ኪም ጆንግ ለደብዳቤዉ ምላሽ ስለመስጠታቸዉ ምንም መረጃ አለመኖሩን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ከሰሞኑ የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለንን ወዳጅነት እናጠናክራለን ማለታቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *