በሰለሞን ቦጋለ ዳይሬክተርነት የተሰራው የራስ መንገድ ፊልም
ነሃሴ 16 በስካይላይት ሆቴል እንደሚመረቅ ያነሳው ተዋናይ እና ዳይሬክተር ሰለሞን ቦጋለ የፊልሙ ገቢ ህብረት ለበጎ የሆስፒታል ግንባታ ይውላል ብሏል።
ከዛሬ ሰባት አመት በፊት የታቀደው ህብረት ለበጎ ሪፈራል ሆስፒታል በ60ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መሆኑንም ተናግሯል።
ለአቅመ ደካሞች በተለይ ደግሞ ከፍለው የህክምና አገልግሎት ማግኘት ለማይችሉ ወገኖች ታስቦ እየተሰራ እንደሆነም አክሏል።
የዚህን ሆስፒታል ግንባታ ለማፋጠን 14 ፕሮጀክቶች መቀረፃቸው የተነሳ ሲሆን የራስ መንገድ ፊልም ደግሞ አንዱ ፕሮጀክት መሆኑ ተነግሯል።
በለገጣፎ እና ለገዳዲ ብቻ ሳይሆን በአራቱም የከተማዋ አቅጣጫ ሆስፒታሉን በመገንባት ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱንም ለማወቅ ችለናል።
ለ 2ሺህ ሰው ቲኬት የተዘጋጀ ሲሆን የአንዱ ቲኬት ዋጋም 2 ሺህ ብር መሆኑን እና እስከ ቅዳሜ ጠዋት ማግኘት እንደሚቻልም ተገልጿል።
ፊልሙ አጠቃላይ 19 የቀረፃ ቀናትን የፈጀ መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።
በእስከዳር ግርማ
ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም











