መንግስት 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ለጨረታ አቀረበ

መንግስት ስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደግል ለማዛወር በወጣው ጨረታ ባለሐብቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ።

መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ የተለያዩ ማሻሻያዎችን አድርጎ ወደ ስራ ገብቷል።

ከዚህ ውስጥም የግሉ ዘርፍ በስኳር ኢንዱስትሪው የሚያደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ በዘርፉ ማሻሻያዎች ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።

ከዚህ አንጻርም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሐብቶች የስኳር ፋብሪካዎችን ወደግሉ ዘርፍ ለማዛወር በወጣው ጨረታ እንዲሳተፉ ጥሪውን አቅርቧል።

ኦሞ ኩራዝ 1፣ ኦሞ ኩራዝ 2፣ ኦሞ ኩራዝ 3 ፣ ኦሞ ኩራዝ 5፣ አርጆ ደዴሳ፣ ከሰም፣ ጣና በለስ እና ተንዳሆ የስኳር ፋብሪካዎች ለጨረታ ቀርበዋል።

ጨረታው ተወዳዳሪነትን እና የስኳር ምርታማነትን በማሳደግ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሟላት ያለመ መሆኑንም ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመላክቷል።

ይህም ኢትዮጵያ ለስኳር ግዢ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት፥ ገቢን ለማሳደግ ብሎም የሸንኮራ አገዳ አምራቾችን ህይዎት ለማሻሻል እንደሚረዳም ታምኖበታል።

ከዚህ ባለፈም ጥሬ እና ያለቀለት የሸንኮራ አገዳ ምርትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት እንደሚረዳም ነው በመግለጫው ያመላከተው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.