ከአንድ የንግድ ድርጅት መጋዘን ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን 226 ልዩ ልዩ ጎማዎች የሰረቁ ተጠርጣሪዎች ተያዙ፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመዉ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ነዉ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳለዉ ከተሰረቁት ጎማዎች አብዛኛውንን ማስመለስ ተችሏል፡፡

በተቋሙ ውስጥ በሚሰሩ ሰራተኞች እና ከውጪ ያሉ ወንጀል ፈፃሚዎች ተባብረው ወንጀሉን መፈፀማቸውን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን አስታዉቋ፡፡

የተሰረቀውን ጎማ ለማስመለስ በተደረገ ጥረት 118 ጎማዎች ማስመለስ እንደተቻለ እና የተለያዬ ተሳትፎ ያላቸው 8 ግለሰቦች ተይዘው ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *