ኩዌት 7 ሺህ 500 የግብፅ ሰራተኞችን ልታሰናብት መሆኗን ገለጸች።

የኩዌት መንግስት 7 ሺህ 500 የሚሆኑ የግብጽ ስደተኞችን ከስራቸው ልታሰናብት እንደሆነ ማሳወቋን ሚድል ኢስት ሞኒቶር ዘግቧል፡፡

ኩዌት በሚቀጥለው ወር 2 ሺ 500 የግብፅ ሰራተኞችን አሰናብታለው ያለች ሲሆን፤ በሚቀጥለው አመት ደግሞ የተቀሩት 5 ሺህ የግብጽ ሰራተኞች ይሰናበታሉ ተብሏል፡፡

የግብጽ ብቻም ሳይሆን ኩዌት ከቀጣዩ አመት ጀምሮ ከሌላ ሃገራት ጋር የሚደረጉ የሰራተኞች ኮንትራት ሙሉ በሙሉ እንደምታቋርጥ አስታውቃለች።

በባህረ ሰላጤዋ ሀገር ኩዌት ግብፃውያን ከጠቅላላው የሃገሪቱ የሰው ሃይል 24 በመቶውን እንሚሸፍኑ መረጃው አመላክቷል፡፡
ይህም በሃገሪቱ ካሉ የስደተኞች ቡድን የሰው ሃይል ከፍተኛውን ቁጥር ይወስዳሉ፡፡


በኩዌት ካለው የሰው ሃይል 77.7 በመቶ በስደተኞች የተያዘ ሲሆን በራሷ ዜጎች የሚሸፈነው 22.3 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *