የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ዳግም የተቀሰቀሰው ትጥቅን ያካተተ ግጭትን እንዲረጋጋ እና የተጀመረው የሰላም ሂደት እንዲቀጥል ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል መልሶ ያገረሸው የትጥቅ ግጭት በእጅጉ እንደሚያሳስበዉ አስታዉቋል፡፡

ከዚህ በፊት የተፈጠረው የትጥቅ ግጭት ተነግሮ የማያልቅ የሰው ልጅ ስቃይ እና ከፍተኛ መሰረተ ልማቶች መውደም ምክንያት መሆኑንም ምክር ቤቱ ገልጿል፡፡

በመሆኑም አሁን ዳግም የተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት እንዲረጋጋና ግጭቱ እንዳይባባስ አፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ ምክር ቤቱ አጥብቆ ያሳስባል ሲል ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከዉ መግለጫ አስታዉቋል።

በተጨማሪም አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁሙ መከበር ለሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት ቀጣይነት እና ለሰላም ሂደቱ ስኬታማነት ወሳኝ እንደሆነ እንደሚያምን ተናግሯል።

ምክርቤቱ አለመግባባቶች በፖለቲካዊ ውይይት መፈታት እንዳለባቸው በጥብቅ እንደሚያምንናለዚህም የሰላም ማስፈን ሂደቱ በአስቸኳይ እንዲቀጥልና ሀገሪቱንና ዜጎቿን ከተጨርማሪ ጥፋት ለመታደግ የሰላም ሂደቱ በቅን ልቦና እንዲካሄድ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.