ቻይና የእስራኤልና ፍልስጤም ግጭት እልባት እንዲያገኝ ጠየቀች፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቻይና ቋሚ ተወካይ ዣንግ ጁን ሃዉስ፣ አለም አቀፉ ማህበረሰብ የእስራኤልና የፍልስጤም ግጭት እልባት እንዲያገኝ ተጨባጭ እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባል ብለዋል፡፡

ዣንግ ግጭቱን ለመፍታት ቀዳሚዉ ጉዳይ ሁለቱም ወገኖች በዲፕማሲያዊ አቅጣጫዎች የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያከብሩ፣እንዲረጋጉ እና እነዚህ ጥረቶች እንዲቀጥሉ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች ወደ ጋዛ እንዲገቡ እና በተቻለ ፍጥነት በእስራኤል የጋዛ እገዳ ሙሉ በሙሉ እንዲቆምም ማሳሰባቸዉን ሲጂ ቲኤን አስነብቧል፡፡

ፍልስጤም አሁን የተወረረችበት ግዛት ዘላቂ እንደማይሆንና አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶት የጉዳዩን መነሻ ሊጋፈጥ ይገባዋል፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉ አሉታዊ ግንኙነት እንዲስተካከልም የሁለት ሀገራት የጋራ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የፍልስጤማዉያን የማይገረሰሱ መብቶች ወደቦታቸዉ ከተመለሱ በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል ያለዉን የተቀናጀ አብሮመኖርና ሰላም መመለስ እንደሚቻል አንስተዋል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.