የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ከዓለም ሃገራት ግንኙነት የተገለለች እንደሆነች የሚነገርላትን ሰሜን ኮሪያን እንዲጎበኙ የሚጠይቅ ደብዳቤ እንደደረሳቸዉ የደቡብ ኮሪያዉ ኬቢኤስ ዘግቧል፡፡
የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስም ሰሜን ኮሪያን ለመጎብኘት ፈቃደኛ ነኝ ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡

ጳጳሶች በምንም ሁኔታ ወደ ሃገሪቷ እንዲገባም ሆነ በቋሚነት እዲቀመጥ ወደማትፈቅደዉ ሰሜን ኮሪያ ጳጳሱ ጉብኝት ሲያደርጉ ይሄ የመጀመሪያቸዉ ነዉ ተብሏል፡፡
በሃገሪቷ ምን ያህል ካቶሊካዉያን እንዳሉና እምነታቸዉን እንዴት እንደሚያካሂዱ በተወሰነ መልኩ እንሚታወቅም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ፖፕ ፍራንሲስ ፒዮንግያንግን መጎብኘታቸዉ በቀጠናዉ ለተከሰተዉ ዉጥረት ሰላም ያመጣል በሚል ተስፋ ተጥሎበታል ሲል ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል፡፡
በቤዛዊት አራጌ
ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም











