ለውጭ ማስታወቂያ የሚሆን መሬት በጨረታ ሊቀርብ ነው፡፡

የውጭ ማስታወቂያ አገልግሎት ለሚሰጡ ድርጅቶች መሬት በጨረታ ሊቀርብላቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡
የውጭ ማስታወቂያ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ድርጅቶች ከዚህ በፊት ባገኙት ቦታ ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን ከዚህ በኃላ ለቁጥጥር እንዲያመች ድርጅቶች ግልጽ እና የታወቀ ቦታ ሊኖራቸው ይገባል ተብሏል፡፡

እንደዚሁም በመዲናዋ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው ከ22ሺህ በላይ የውጭ ማስታወቂያዎች ሊነሱ ነው፡፡

ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው የውጭ ማስታወቂያዎች እንደሚነሱ ነው የተገለጸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የውጭ ማስታወቂያ ቁጥጥር ዳሬክተር የሆኑት አቶ አዲሱ መለሰ በሚቀጥለው 2015 አመት ከውጪ ማስታወቂያ ጋር በተያያዘ ሰፊ ስራ ለመስራት ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ከተማዋ ከዚህ በፊት ያልነበራት የውጭ ማስታወቂያ መመርያ እና ደንብ ማዘጋጀቷን የተናገሩት አቶ አዲሱ ለ6ሺህ 992 ድርጅቶች የውጭ ማስታወቂያ ፍቃድ ይሰጣል ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.