ቴሌ ብር ከ73 አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በትስስር እየሰራ ይገኛል ።

ቴሌ ብር አገልግሎቱን መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ73 አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በትስስር እየሰራ መሆኑን የቴሌ ብር መተግበሪያ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ብሩክ አዳነህ ተናግረዋል ።

የቴሌ ብር መተግበሪያ አገልግሎቱን መስጠት የጀመረው ከ15 ወራት በፊት መሆኑ ተገልጿል ።

ከዛም ጊዜ አንስቶ 67.2 ሚሊዮን ደንበኞችን ማፍራት የቻለ ሲሆን ፤46 ቢለየን ብር ዝውውር ማድረግ መቻሉን አቶ ብሩክ ጨምረው ገልፀዋል ።

ቴሌ ብር የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራቸውን ቀልጣፈና ፈጣን ከማድረግ ባለፈ፤ ማህበረሰቡን ያስመረሩ ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ትልቅ እድልን መፍጠር ችሏል ።

ከምን በላይ ከሰነዶች ጋር ተያያዣነት ያላቸውን አገልግሎቶችን ከእጅ ንክኪ ነፃ በማድረግ ከሙስና የጠራ አሰራር እንዲፈጠር ሆኗል ።

ይህንንም ተግባር አጠናክሮ ለማስቀጠል ኢትዮ ቴሌኮም ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በትስስር ለመስራት የዉል ስምምነት አድርገዋል ።

ይህም ኢትዮ ቴሌኮም በትስስር አብሮ የሚሰራቸውን የአገልግሎት ተቋማት 74 ያደርሰዋል ።

በውል ስምምነቱ ላይ የተገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ስራአስኪያጅ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ ተቋሙ ባጭር ጊዜ ውስጥ እያሳየ የመጣውን አገልግሎን የማዘመን ስራን አድንቀዋል ።

አሁንም ሰዎችን የሚያጉላሉ እና የሚያሰለቹ አሰራሮችን ለመቅረፍ በንቃት እንሰራለን ብለዋል።

በሃገራችን የቴሌ አገልግሎት 99.1 አንድ መቶ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *