የኬኒያ ፍርድ ቤት ራይላ ኦዲንጋ በምርጫ ውጤት ላይ ያቀረቡትን ክስ ማየት ጀምሯል፡፡

ሚሊያም ሩቶ አሸንፈዋል ተብሎ የነበረው የኬኒያ ምርጫ በተፎካካሪው ራይላ ኦዲንጋ ተቃውሞ እንደገጠመው አይዘነጋም፡፡

የምርጫ ውጤቱ ተጭበርብሯል ያሉት ራይላ ኦዲንጋ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡
ራይላ በፈረንጆቹ 2017 በተመሳሳይ መልኩ የምርጫው ውጤት አልቀበልም ብለው ፍድቤት መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

ለአምስት ተከታታይ አመታት በምርጫ ተወዳድረው ያልተሳካላቸው ራይላ ኦዲንጋ ፍትህ እንፍልጋለን እያሉ ይገኛሉ፡፡

በማርታ ኮሜ የሚመራው የኬኒያ ፍርድ ቤት ራይላ ኦዲንጋ ያቀረቡትን ክስ እየመረመሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

እጩ ተወዳዳሪው እና ደጋፊዎቻቸው የክስ ሂደቱ እስኪያልቅ ድረስ ከጸብ አጫሪነት ሊቆጠቡ ይገባልም ብለዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በ2017 ከነበረው ምርጫ ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ልጆቻቸውን በሞት ያጡ ቤተሰቦች ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

አሁን በሀገራችን ሌላ ችግር እንዲከሰት አንፈልግም የሚሉት እነዚህ ቤተሰቦች መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው በተረጋጋ ሁኔታ የክሱን ውጤት እንዲጠብቁም አሳስበዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ ዘግቦታል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *