የጎንደር ዩንቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መርሐ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

የጎንደር ዩንቨርስቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የትምህር መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 5ሺህ 5 መቶ 27 ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል ።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን የዘንድሮ ተመራቂዎቹ ወቅታዊውን ችግር ተቋቁመው ለዚህ በመብቃታቸው ልዩ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

ተመራቂዎቹ ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር ከመፍታት አኳያ ትልቅ የቤት ስራና ኃላፊነት እንዳለባቸው ዶክተር አስራት አሳስበዋል ።

አንድነታችን የድላችን ምንጭ ነው ያሉት የዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት ፣ ሁላችንም ለኢትዮጵያ ሠላምና ደህንነት በጋራ ልንረባረብ ይገባል ብልዋል ።

ተመራማሪዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታታ፣በሁለተኛና በሶስቸኛ ዲግሪ መርሃግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

የጎንደር ዩንቨርስቲ ከ3 መቶ 20 በላይ የትምህርት መርሐግብሮች እንዳሉት ተነስቷል ።

በተጨማሪም 10ሺህ 5 መቶ 86 መምህራንና ሥራተኞች እንዳሉትም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል ።

የጎንደር ዩንቨርስቲ ከ 67 አመት በፊት በጤናው ዘርፍ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው።

በአባቱ መረቀ

ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.