በካታር የዓለም ዋንጫ ‹‹በተመረጡ የስታዲየም ክፍሎች›› አልኮል ይቀርባል፡፡

በ2022ቱ የዓለም ዋንጫ ‹‹ በተመረጡ የስታዲየም ክፍሎች›› አልኮል እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ተናግረዋል ፡፡
የፊፋ የዓለም ዋንጫ በሙስሊም ሃገር በመካከለኛው ምስራቅ ሲከናወን ይህኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፡፡
በእስልምና ደግሞ አልኮል መጠጣት ይከለከላል ፡፡

በዋና ከተማዋ ዶሃ 40 ሺ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ለደጋፊዎች በተከለለ ቦታ ግን መጠጥ እንደሚሸጥ ማረጋገጫ ተሰጥቷል ፡፡

‹‹ሰዎች ወደዚህ መጥተው ፈጽሞ የማይረሱትን ተሞክሮ ገብይተው እንዲሄዱ እንፈልጋለን ›› በማለት ዋና ስራ አስፈጻሚው ናስር አል ካተር ለቢቢሲ ተናግረዋል ፡፡
አልካትር ‹‹ የአልኮል ስትራቴጂያችንን በማጠናቀቅ ላይ ነን›› እስከዚያው ግን በስታዲየሙ ዙሪያ ደጋፊዎች መጠጥ የሚጎነጩበትን መንገድ ይፋ አድርገናል ብለዋል ፡፡
ፊፋ የጨዋታ መግቢያ ትኬት የያዙ ደጋፊዎች ከጨዋታው መጀመር እና መጠናቀቅ በኋላ በስታዲየሙ ዙሪያ መጠጥ የሚጎነጩበት አማራጭ እንደሚኖራቸው አሳውቋል ፡፡

በአቤል ጀቤሳ
ጳጉሜ 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *