ቱክል ተሰናበቱ

የቼልሲው አሰልጣኝ ቶማስ ቱክል ከትላንቱ የቻምፒየንስ ሊግ ሽንፈት በኋላ ተሰናብተዋል ፡፡ የቀድሞው የቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ፒኤስጂ አሰልጣኝ ከ20 ወራት በኋላ የስታምፎርድ ብሪጅ እህል ውሃቸው ተቋርጧል ፡፡

ጀርመናዊው በሰማያዊዎቹ ቤት ባሳለፉት ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፋቸው ይታወቃል ፡፡ ይህንን ያደረጉት በተሸሙ በአራት ወራቸው መሆኑ አስመስግኗቸው ነበር ፡፡ የዩኤፋ ሱፐር ካፕ እና የክለቦች የዓለም ዋንጫንም አሸንፈዋል ፡፡

የዘንድሮውን የውድድር ዘመን የጀመሩበት መንገድ ግን ትችት ሲያሰነዝርባቸው ነበር ፡፡ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ለተጫዋቾች ዝውውር ከፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሁሉ ቀዳሚ የሆነው ክለብ በቡድኑ ላይ ከፍተኛ መሻሻል ባለማሳየቱ አሰልጣኙ የስንብት ደብዳቤ እንዲቆረጥላቸው አስገድዷል ፡፡

ቶድ ቦህሊ አዲስ አሰልጣኝ እስከሚሾም ድረስ የአሰልጣኝ ቡድኑ አባላት በሃላፊነት እንዲመሩ ወስነዋል ፡፡
አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ‹‹ትክክለኛው ጊዜ ነው ›› ሲሉም ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል ፡፡

በአቤል ጀቤሳ

ጳጉሜ 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *