ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች መስፋፋት ምክንያት ከ 31 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱ ተገለፀ፡፡

ኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች አምራች ዜጎቿን እያጣችና የኢኮኖሚ እድገቷ እየተገታ ከመሆኑም በላይ ለነዚህ ህመሞችም በዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር እንደምታወጣ የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር አስታዉቋል።

ማህበሩ ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ በላከው መግለጫ ላይ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች አንዱና ዋነኛ አጋላጭ መሆኑን ገልጿል።

በኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ብዙ ሰዎች በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን ገዝተው በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ የገለፀው ማህበሩ እነዚህም የምግብ አይነቶች በፍጥነት ወደ ገበያ እየገቡ መሆኑን አመላክቷል።

እ.ኤ.አ. በ 2019 በሀገሪቱ የተመዘገበው 39.2% አጠቃላይ ሞት ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች እንደ ልብ ድካም ፣ ስትሮክ ፣ የስኳር በሽታ እና ካንሰር ባሉ ሥር በሰደዱ በሽታዎች ምክንያት ነው መባሉን ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡

በ2017 ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች አጠቃላይ የመንግስት ወጪ 4.4 ቢሊዮን ብር ነበር። በ2014ዓ.ም ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች መስፋፋት ምክንያት (ቀጥታ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ወጪ) 31.3 ቢሊዮን ብር የኢኮኖሚ ኪሳራ አጋጥሟል ።

ይህም ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 1.84 በመቶ አካባቢ እንደሚይዝ የማህበሩ መግለጫ ያስረዳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.