ሩሲያ ከዩክሬን በነጠቀቻቸዉ አራት ግዛቶች ህዝበ ዉሳኔ ማካሄድ ጀመረች፡፡

የሩሲያ ጦር ከዩክሬን በነጠቃቸዉ አራት ግዛቶች ህዝበ ዉሳኔ መጀመሩን የአገሪቱ መንግስት አስታዉቋል፡፡ህዝበ ዉሳኔዉ የሚካሄደዉ በ ሉሃንስክ፤ ዶኔስክ፤ በኬርሶንና በዛፖርዢያ ግዛቶች ነዉ፡፡

ሂደቱ እስከ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ድረስ እንደሚቀጥልም ሞስኮ አስታዉቃለች፡፡ምዕራባዉያኑ ግን ህዝበ ዉሳኔዉን ለይስሙላ የሚደረግ ሲሉ አጣጥለዉታል፡፡

ሩሲያ ከስምንት አመት በፊት ከዩክሬ በወሰደችዉ ክረሚያ ግዛት ተመሳሳይ ህዝበ ዉሳኔ አድርጋ ማጠቃለሏ የሚታወስ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ

መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.