በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አምስት ሰዎች ተገደሉ፡፡

በትላንትናዉ እለት የሸኔ የሽብር ቡድን በወረዳው ባደረሰው ጥቃት አምስት ሚሊሻዎች መሞታቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
የአማሮ ልዩ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንፔክተር አራርሶ ነጋሽ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በአካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያሉትን ግድያዎች በመፈጸም ላይ ያሉት ከምዕራብ ጉጂ ገላና ወረዳ የሚነሱ የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው፡፡

ትላንት የተከሰተው የጸጥታ ችግርም ጠንሳሾቹ እነርሱ መሆናቸው የገለጹት አራርሶ ነጋሽ፣ በወረዳው አሁንም ከፍተኛ የጸጥታ ችግር መከሰቱን ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው እለት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተውጣጡ አካላት በወረዳው ከዚህ በፊት የተከሰተውን የጸጥታ ችግር በተመለከተ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ለመምከር እያቀኑ በነበረበት ጊዜ ነው ጥቃቱ የደረሰው፡፡
በአካባቢው ከፍተኛ “የታጣቂዎች ክምችት” እንዳለ ከነዋሪዎች መስማታቸውንና ይህንኑም ዛሬ ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሰው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ማረጋገጣቸውን ነግረዉናል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *