ሳዑዲ አረቢያ በመዲና ዉስጥ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ማግኘቷን አስታዉቃለች፡፡
የተገኘዉን ከፍተኛ የወርቅ ክምችት የተቀረዉ ዓለምም እንዲጠቀምበት ዕድሎችን እያመቻቸች መሆኗንም ገልጻለች፡፡
ሳዑዲ አረቢያ በእስልምና ቅዱሷ ከተማ ተብላ በምትጠራዉ መዲና ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የወርቅ እና መዳብ ክምችት ማግኘቷን የገለጸዉ የሀገሪቱ ጅኦሎጂካል ሰርቬይ ነዉ፡፡
የዚህ ክምችት መገኘት የሀገሪቱን በነዳጅ ላይ ጥገኛ የሆነ የኢኮኖሚ ዘርፍ ወደ ሌላ መስመር ያሸጋግርላታል ሲልም ያለዉን ተስፋ ገልጿል፡፡

እንደ አል አረቢያ ሪፖርት የሳዑዲ ባለስልጣናት የተገኘዉ ወርቅ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የ5 መቶ 33 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሳብ ይችላል ፤ ለ4ሺህ ዜጎችም የስራ እድል ይፈጥራል ሲሉ ከአሁኑ ተስፋቸዉን ጥለዉበታል፡፡
የሀገሪቱ የአፈር እና የከበሩ ማዕድናት አጥኚዎች ቡድን እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ከ 5 ሺህ 3 መቶ በላይ የሆኑ የማዕድን ስፍራዎች አሏት፡፡
በነዚህ ስፍራዎችም ብረት፣ የህንጻ መሳሪያዎች፣ የማስጌጫ ድንጋዮች እና ዉድ የሆኑ የጌጣጌጥ ድንጋዮች ይገኙበታል ሲል የዘገበዉ ሚረር ነዉ፡፡
በእስከዳር ግርማ
መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም











