በአቃቂ ቃሊቲ የእሳት አደጋ የሰው ህይወት አጠፋ::

ዛሬ ሌሊት 7 ሰዓት ከ44 ደቂቃ ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 13 ቱሉዲምቱ አካባቢ የተለያዩ አነስተኛ የንግድ አገልግሎት የሚሰጡ 15 የሚሆኑ በላስቲክ፣ በሸራና አነስተኛ ቁሳቁስ ተሰሩ መጠለያዎች በእሳት አደጋ ወድመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዕሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንዳስታወቁት፥ እሳቱ ወደሌላ ስፍራ ሳይዛመት በቀላሉ መቆጣጠር ተችሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.