በአዲስ አበባ ከተማ መስከረም 17 ቀን የሚከበረው የመስቀል በዓል በሰላም ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተወሰነ።

የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ እሁድ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 17 ቀን ማታ 12:00 ድረስ ምንም አይነት የሞተር እንቅስቃሴ በከተማዋ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚህም ኤጀንሲው የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ ብሏል፡፡

ይሄንን ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ማለቱን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.