የመቋቋሚያ ደንብን እንዲሁም የቴሌኮም ገበያው ለውድድር ክፍት መሆኑንም ታሳቢ በማድረግ የ3 አመት ስትራቴጂው ተዘጋጅቷል ነው የተባለው።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ይህ ሊድ /መሪ የተሰኘ የዕድገት ስትራቴጂ ከኮሚኒኬሽን አገልግሎት ባሻገር የዲጅታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶችን የሚያቀርብ ስትራቴጂ መሆኑም ገልፀዋል።
በዚህ ስትራቴጂ ውስጥ ባለፉት 128 አመታት ኩባንያው ይዞት የነበረውን አላማ ፣ተልዕኮ እና እሴቶች በውድድር ገበያው ቀዳሚ የመሪነት ስፍራ እንዲኖረው በሚያስችል መልኩ መቀየራቸውንም ገልጸዋል።
በበጀት አመቱም በአጠቃላይ 8 ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል የሞባይል ኔትወርክ አቅም መገንባት እንደ ዕቅድ መያዙንም አንስተዋል።
በዚህም የደንበኞች ብዛትን በ10.3 በመቶ በመጨመር 73.5 ሚሊየን ማድረስ ፣ በሞባይል ደግሞ 10.5 በመቶ በመጨመር 71 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱንም አክለዋል።
በተጨማሪም የፊክስድ ብሮድባንድ ደንበኞችን ደግሞ በ37.4 በመቶ በመጨመር 696.7ሺህ በማድረስ የቴሌኮም ስርፀት መጠንን 68 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ከገቢ አንፃርም በ2015 በጀት አመት አጠቃላይ የገቢ መጠንን በ22.4 በመቶ በማሳደግ 75.05 ቢሊየን ብር ለማድረስም እቅድ መያዙን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።
በቅርቡም ከኮሚኒኬሽን ባሻገር በሚል የክላውድ ሶሉይሽን ፣ ስማርት ሲቲ ፣ስማርት አግሪካልቸር ፣ ስማርት ኢጁኬሽን ፣ ስማርት ኸልዝኬር ፣ስማርት ሆም እና ኢንተርፕራይዝ ሶሉይሽን የተሰኙ አገልግሎቶችን ይፋ እንደሚያደርግም ተገልጿል።
በእስከዳር ግርማ
መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም











