ኢትዮ ቴሌኮም አዲሱን ሊድ የተሠኘ ስትራቴጂውን አስተዋወቀ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ለቀጣዮቹ ሶስት አመታት የሚቆየውን ሊድ የተሠኘውን አዲሱን ስትራቴጂ እና የ2015 በጀት አመት የስራ እቅዱን በዛሬው እለት እያስተዋወቀ ይገኛል።
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ እስከ 2017 የሚያገለግለውን አዲሱን ስትራቴጂ እና የበጀት አመቱን እቅድ ለመገናኛ ብዙሀን እያቀረቡ ነው።

እ.ኤ.አ ከ2019 ጀምሮ እስከ ሰኔ 2022 ድረስ ሲያገለግል የነበረው ብሪጅ የተሠኘው ስትራቴጂ ኩባንያው ብቁ ፤ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ የቴሌኮም ኦፕሬተር ለመሆን እያደረገ ላለው ጉዞ መሠረት የጣለ መሆኑን ወ/ት ፍሬህይወት ተናግረዋል።

ብሪጅ ስትራቴጂ የኩባንያው የሪፎርም ውጤት መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በቆይታው ኩባንያውን በሁሉም የተሠማራባቸው መስኮች ውጤታማ ማድረግ የቻለ እና ከመደበኛ የሲም ካርድ ሽያጭ ባሻገር በሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶች እንዲሰማራ አቅም የፈጠረ ነው ብለዋል።
ሊድ ስትራቴጂ ከሐምሌ 2014ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.