የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ዜጎችን መርዳት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ::

የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ኢጋድና አክሽን ፎር ዘኒዲ ኢን ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያንና የደቡብ ሱዳንን ዜጎች ተጠቃሚ ያደርጋል ያሉትን ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

የኢጋድ ዋና ፀኃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ፖሮጀክቱ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ ለገጠማቸው የሁለቱ አገራት ዜጎች ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ ቀውሶች እየተበራከቱ እንደመጡም ዋና ፀኃፊው አስታወቀዋል።

ስደትና መፈናቀል የአፍሪካ ቀንድ ችግር መሆናቸውን የጠቀሱት ዶክተር ወርቅነህ፣የቀጠናው የሠላም ሁኔታ መዳከም ምክንያት ነው ብለዋል።

በዚህም በርካታ ዜጎች ለስደትና ለመፈናቀል መዳረጋቸው ተነስቷል።

በደቡብ ሱዳንና በኢትዮጵያ ጠረፋማ አካባቢ ለሚገኙ ዜጎች የሰብአዊ ዕርዳታ እንዲያገኙ ይሰራልም ተብሏል።

አክሽን ፎር ዘኒዲ ኢን ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ አቶ ሳልሁ ሱልጣን ፣ለሰበአዊ ቀውስ የተጋለጡ ዜጎችን የመርዳቱ ስራ ተጠናከሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት የድርጅቱ የመጀመሪያው ድንበር ተሻጋሪ የሰባዊ ድጋፍ እንደሆነም ታውቋል።

የሰብአዊ ቀውሶችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስና የመልሶ ማቋቋም ስራ እንደሚሰራም ድርጅቱ አስታውቋል።
አክሽን ፎር ዘኒዲ ኢን ኢትዮጵያ ከ10 ዓመት በፊት የተቋቋመ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ነው።

በአባቱ መረቀ
መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.