የጸጥታ ችግር ያለባቸዉ አካባቢ ተማሪዎች ፈተናዉን በሁለተኛዉ ዙር ይወስዳሉ፡፡

የትምህርት ሚንስቴር የ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ መግለጫ እየሰጠ ነዉ፡፡

ሚንስቴሩ እንዳለዉ፣ በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላምና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉ እንዲሁም ከአገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር ፈተና እንምደሚዘጋጅላቸዉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

ይህም ቁጥራቸዉ በአጠቃላይ 56 ሺሕ እንደሚደርስ ሚንስቴሩ ገልጿል፡፡

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 26-28 ወደሚፈተኑባቸው ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን፤ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 02 ፈተና ወስደው ከጥቅምት 03 ጀምሮ ወደመጡበት እንደሚመለሱ ተጠቅሷል።

በሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 5 አስከ ጠቅምት 6 ወደ ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከጥቅምት 8 እስከ ጠቅምት 11 ፈተና ወስደው ከጥቅምት 12 ጀምሮ ወደመጡበት የሚመለሱ ይሆናል ተብሏል።

ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እና ሌሎችም ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቁሶችን መያዝ እንደማይችሉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

አሚኮ እንደዘገበዉ ተማሪዎችን ወደ ተመደቡባቸው አካባቢዎች የሚያደርሷቸው የክልል የፀጥታ አካላት ሲሆኑ፤ በዩኒቨርሲቲዎች የጥበቃና ፍተሻ ሥራን የሚሰሩት የፌዴራል ፖሊስ አባላት መሆናቸውንም የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.