የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለአትሌት ደራርቱ ቱሉ እና አሰልጣኝ ሁሴን ሼቦ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለአመራሮቹና አባላቶቹ በህግ ማስከበር ዘመቻ እና የላቀ ተግባር ለፈፀሙ እውቅናና የማእረግ እድገት በሰጠበት ስነስርዓት አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እና አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ሼቦ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ አግኝተዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና በርካታ አትሌቶችን ያፈሩት አንጋፋው አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ሼቦ ደግሞ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ሹመት ተሰጥቷቸዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለአትሌቲክስ ጀግኖቹ ለሰጠው እውቅና ማቅረቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *