ፖፕ ፍራንሲስኮ ፑቲን አመጽ እና ሞትን እንዲስቆሙ ተማጸኑ::

ሮማዉ ሊቃነ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በሩሲያና በዩክሬን መካከል ሰባት ወራትን ያስቆጠረዉን ጦርነት በምንም መልኩ ተቀባይነት እንደሌለዉ ገልጸዋል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን የምታርገዉን ጥቃት እና የማጥፋት ትግል እንድታቆም ለፑቲን ተማጽኗቸዉን አሰምተዋል፡፡

የአለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ፖፕ ፍራንሲስ የዩክሬን አራት ክልሎችን መቀላቀል ለኑክሌር መስፋፋት አደጋ አለዉ ሲሉ አዉግዘዋል፡፡
ፑቲን በሴንት ፒተር አደባባይ ለዩክሬን በተሰጠ አድራሻ ላይ ስለራሳቸዉ ሰዎችም እንዲያስቡ አሳበዋል፡፡

አንድ የቫቲካን ባለስልጣን የጳጳሱን ንግግር አስደንጋጭና በ1962 በኩባ ሚሳኤል ቀዉስ ዉስጥ ርእሰ ሊቃነ ጳጳስ ጆን ፖል ያቀረቡት የሰላም ጥሪ የሚያስታዉስ ነዉ፣ ይህ ንግግራቸዉም ለወገኖቻቸዉ ያላቸዉን ፍቅር የሚያሳይ ነዉ ሲሉ መናገራቸዉን አልጀዚራ አስነብቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *