የኢትዮጵያ መንግስት፤ የኢትዮጵያ ወዳጆች ወይም ” የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ህገመንግስት እናከብራለን ” የሚሉ ወገኖች ከሰላም ንግግሩ ጋር በተያያዘ የቃላት አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲደረጉ አሳሰ
ፌዴራል መንግስት ማሳሰቢያውን ያወጣው በስሩ ባለው የ ” ወቅታዊ ሁኔታዎች መረጃ ማጣሪያ ” በኩል ነው።
የመረጃ ማጣሪያው እንደ ” የትግራይ መንግስት (Government of / state of Tigray ” ወይም ፣ ” የትግራይ የውጭ አገልግሎት / Tigray External Service ” የመሳሰሉ አገላለጾች ተራ ስህተቶች ሳይሆኑ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆናቸው ሊፈተሹ ይገባል ብሏል።
የኢትዮጵያ ወዳጆች ወይም ” የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና ሕገ መንግሥት እናከብራለን ” የሚሉ ወገኖች ሁሉ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት በቅርቡ በሚደረገው የሰላም ንግግር ሕገ-ወጥ ቃላትን / አገላለፅን ከመጠቀም ይቆጠቡ ሲል አስገንዝቧል።
” ከዚህ የሰላም ንግግር አንፃር ወዳጆቻችን እና አጋሮቻችን ማስታወስ ያለባቸው ሁለቱ ወገኖች በመሰረታዊነት ልዩነት ያላቸው መሆኑን ነው ” ያለው ይኸው የመረጃ ማጣሪያ ፤ ” አንዱ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ፣ ህጋዊ መንግስት እና ሌላኛው ‘ ህወሓት ‘ የታጠቀ ቡድን ነው ” ብሏል።
እንደዚሁም እንደ ” የትግራይ አስተዳደር / Tigray Administration ” ወይም ” የትግራይ ክልል መንግስት / Regional Government of Tigray ” የመሳሰሉ አገላለፆችም ተቀባይነት የላቸውም ሲል አሳውቋል።
ምክንያት ያለውም ፤ ” በትግራይ ክልል ውስጥ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት የተመረጠ አካል ስለሌለ ነው ” ሲል አስረድቷል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም











