ቻይና አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችዉን ህጋዊ ያልሆነ ማዕቀብ እንደምትቃወም ገለጸች፡፡

ቻይና አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችዉን ህገወጥ ማዕቀብ እንደምትቃወም በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በኩል ገልጻለች፡፡

በኢራን አንዲት ወጣት በፖሊስ ግድያ ከተፈጸመባት በኋላ፣ ኢራናዊያን ወደ አደባባይ በመዉጣት መንግስታቸዉን እየተቃወሙ ሲሆን በዚህ ምክንያትም አሜሪካ በኢራን ላይ ማዕቀብ ጥላለች፡፡

ቻይና የአሜሪካን ማዕቀብ በእጅጉ ትቃወማለች ያሉት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ፣ በተጨማሪም በየትኛዉም ሁኔታ ቢሆን በሌሎች ሀገራት የዉስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባትንም እንቃወማለን ነዉ ያሉት፡፡

በዲሞክራሲ እና ሰብዓዊ መብቶች ስም በየሀገራት ጉዳይ ጣልቃ የሚገባዉን ጉዳይ የቻይና መንግስት አይደግፈዉም ሲሉም አክለዋል፡፡

የኢራን ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ‹‹በየቀኑ በአዳዲስ ጉዳዮች ላይ ኢራን ላይ የሚጣል ማዕቀብ ይጣላል፣ በዚህኛዉ ዙር ደግሞ የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር፣ የዉስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም በሌሎች አምስት የኢራን ሚኒስቴሮች ላይ አሜሪካ ማዕቀብ ጥላለች›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በ22 ዓመቷ ኢራናዊት ማህሳ አሚኒ ሞት ምክንያት ወደ አደባባይ የወጡት ተቃዋሚዎች በተወለደችበት ኮርድስታን ከተማ ጀምረዉ ዋና ከተማዋ ቴህራን ድረስ ተቃዉሟቸዉን እያሰሙ መሆኑን ፕሬስ ቲቪ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ጥቅምት 01 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *