ወጣቶች በብሄራዊ ምክክሩ ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ ከማድረግ ተገድበዋል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በሀገሪቱ ለሚካሄደው አገራዊ ምክክር ሂደት ለወጣቶች ትኩረት አልተሰጠም ሲል ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

አገራዊ ውይይቱ አካታች ካልሆነ ውጤታማነቱን አጠያያቂ ያደርገዋል ያለው ምክር ቤቱ፣ እንደ ሀገር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በውይይቱ ላይ ሊካተት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳሬክተር አቶ ሄኖክ መለሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ እስካሁን ባለው ሂደት የሲቪል ማህበራት የወጣቶች መዋቅር በብሄራዊ ውይይቱ ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ ከማድረግ የሚገድባቸው ሁኔታዎች መታየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ እነዚህን ክፍተቶች ለመቅረፍም ከወጣቶች ጋር በመተባበር የወጣቶች የሲቪል ማህበራት ህብረት ለሀገራዊ ውይይት እንዲመሰረት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ የህዝብ ቁጥሯ 70 ከመቶ ያህሉ ከ25 አመት በታች የሚሆኑት ወጣቶች እንደመሆናቸው መጠን በሀገሪቱ ጉዳዮች ሊካተቱ ይገባል ብለዋል፡፡

የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑትን ወጣቶች በሚመለከታቸው ሀገራዊ ጉዳች ሁሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማበረታታት ያስፈልጋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 01 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *