የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አልበርት ፋሂሚ ፓዴክ ስልጣናቸው መልቀቃቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታወቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን የለቀቁት በሀገሪቱ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ በመራዘሙ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
አልበርት ፋሂሚ ፓዴክ ባሳፍነው የፈረንጆቹ 2021 ላይ ነበር ወደ ስልጣን የመጡት፡፡
ቻድን ለ30 አመታት ከመሩት ኢድሪስ ዲቤ ከዚህ በፊትም በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አልበርት ፋሂሚ ከ2016 እስከ 2018 ድረስም በስልጣን አገራቸውን አገልግለዋል፡፡
በድጋሚ 2021 ላይ ወደ ስልጣን የመጡት ፋሂሚ በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና ለመግታት ቁርጠኛ መሆናቸውን ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡
ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሰቡትን ሳያሳኩ በገዛ ፍቃቸው ስልጣን ለመልቀቅ ወስነዋል ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ.ም











