አዋሬ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡

መስከረም 3 /2015 ሌሊት 9:15 በየካ ክፍለከተማ ወረዳ 6 አቧሬ አካባቢ አገልግሎቱ የእንጨት መሰንጠቂያ እንዲሁም የቤትና የቢሮ እቃዎች ማምረቻ በሆነ ድርጅት ላይ ድንገተኛ የአሳት አደጋ ተከስቷል፡፡

በእሳት አደጋው 25 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ሲወድም በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ድርሷል፡፡

ጉዳት ከደረሰባቸዉ ሰራተኞች መካከል አንዱ የእሳት አደጋ ሰራተኛ መሆኑን ከእሳትና ድንገተኛ አቶ ንጋቱ ማሞ ለጣቢያችን ነግረውናል።

እሳቱ በአቅራቢያዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ተዛምቶ በሰዉና በንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ የአካባቢዉ ማህበረሰብና የጸጥታ ኋይሎችን በማሳተፍ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውንም አቶ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ሂደትም 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን የተቻለ ሲሆን በሰዉ ህይወት ላይ ምንም ጉዳት እንዳይደርስ ማድረግ ተችሏል ብለውናል።
አደጋዉን ለመቆጣጠርም 11 የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና 2 አምቡላንስ አነዲሁም 84 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና አመራሮች መሳተፋቸውን የነገሩን አቶ ንጋቱ እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠርም አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ መፍጀቱን ሰምተናል።
በሌላ በኩል ዛሬ ማለዳ 1:55 ላይ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ ድሬ አካባቢ በፍራሽና ጄኔሬተር መጋዘን ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 100 ሺህ ብር የተገመተ ንብረት ሲወድም እሳቱ ተስፋፍቶ የበለጠ ጉዳት ሳይደርስ ንብረቶቹን ከመጋዘኑ በማዉጣት እሳቱን በቀላሉ ለመቆጣጠር መቻሉንና አደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አለማድረሱን ነግረዉናል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 03 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.