ከ100 ሚሊዮን በላይ የህዝብ ቁጥር ያላት ኢትዮጵያ የሕይወት መድን ዋስትና የገባው ከአምስት በመቶ አይበልጥም ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ ከ18 በላይ የመደህን ዋስትና አገልግሎት የሚሰጡ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ያሉ ሲሆን፣በነዚህ ኩባንያዎች ውስጥ የሕይወት መድህን ዋስትና የገቡ አምስት ከመቶ ብቻ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ መድህን ሰጪዎች ማህበር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው፣ የህይወት ዋስትና የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

ይህ የተባለው የኢትዮጵያ መድህን ሰጪዎች ማህበር ብሩህ ከተሰኝ ተቋም ጋር አብረው ለመስራት በተስማሙበት ወቅት ነው፡፡

እነዚህ ሁለት ተቋማት የመድህን አገልግሎት በሚሰጡ ሰራተኞች ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት የስልጠና መርሃግብር ለመስጠት ተስማምተዋል፡፡
በስምምነታቸውም ሰልጣኞች የክፍያ ስርአት ሂደት ሕይወት ነክ ያልሆኑ የመድህን አገልግሎት እና በውል አሰጣጥ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 03 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.