የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ እጩዎችን አቅርበዋል።
በዚህም፥
1ኛ. ዶክተር ቀንዓ ያደታ- የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ
2ኛ. አቶ ምትኩ አስማረ – የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
3ኛ. ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ – የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ
4ኛ. ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ – ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ኃላፊ
5ኛ. ዶክተር ጀማሉ ጀንበር – የህዝብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር
6ኛ. አቶ ጀማል ረዲ – ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር
ሆነው እንዲሾሙ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማው ምክር ቤት ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱ የስራ ኃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል።
ተሿሚዎች በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።











