የ40/60 እና 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም ከምን ደረሰ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲ አዳነች አቤቤ እንዳሉት በ40/60 እና 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም እጣ ለባለ እድሎች የማውጣት ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

ከንቲባዋ 3ኛው የአዲስ አበባ ምክር ቤት 2ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ለም/ቤቱ የ 2015 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርታቸው በቤት ልማት ፕሮግራም የህብረት ሥራ ማህበራት አማራጭ ቤቶችን ጨምሮ ከመንግስትና የግል አልሚዎች ጋር በአጋርነት መስራት የሚያስችል አሰራር በመከተል የቤት ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን የኤ ኤም ኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ከዚህ በፊት በ40/60 እና 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም እጣ በማውጣት ሂደት ያጋጠመውን ችግር የሚቀርፍ የእጣ ማውጣት ስርዓት በመከተል ለባለ እድሎች እጣ የማውጣት ሂደት በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.