በአፍሪካ ህብረት አመቻችነት የሚደረገው የመንግስትና የሕወሃት የሰላም ንግግር ለመጭው ሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም መጠራቱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡
በቀረበው የሰላም ውይይት ላይ መንግስት ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ይሁን እንጅ አንዳንዶች መንግስት በሚወስደው “ራስን የመከላከል እርምጃ” ላይ ሃሰተኛ ውንጀላዎችን በማሰራጨት የተጀመረውን የሰላም ውይይት ለማደናቀፍ እየጣሩ መሆኑን በመግለፅ ወቅሰዋል፡፡
የሰላም ንግግሩ ለመጪው ሰኞ የተቀጠረው ከዚህ ቀደም የአፍሪካ ህብረት ከሁለት ሳምንት በፊት ንግግሩን ለማስጀመር ያስተላለፈው ቀጠሮ ከተሰረዘ በኋላ ነው፡፡
በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም











